የብድር አገልግሎት አይነቶች

1.በተቋሙ የሚሠጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

በአዲስ አበባ ከተማ እና በአካባቢዋ በሚገኙ ልዩ የኦሮሚያ ዞኖች ባሉ አማካይ ቦታዎች በተከፈቱ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ አገልግ/መስጫ ቅ/ጽ/ቤቶች የሚሰጡ

ዋና ዋና አገልግሎቶች፡-

1. የቁጠባ አገልግሎት

2. የብድር አገልግሎት

3. የማይክሮ ኢንሹራንስ አልግሎት

4. የሶስተኛ ወገን ገንዘብ አስተዳደር አገልግሎት

5. የምክር አገልግሎት

6. የመሳሪያ ሊዝ ብድር አገልግሎት

7. የሞባይልና ወኪል ባንኪንግ አገልግሎት

2. የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

- ግለሰቦች

- የግሉ ንግድ ማህበረሰብ

- ህዝባዊ ድርጅቶች

- የሀይማኖት ተቋማት

- የሙያ ማህበራት፣ እድሮች፣ ሌሎች የማህበራዊ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ማህበራት

- የህብረት ስራ ማህበራት ፡ ሲሆኑ የቁጠባ ሂሳብ ለማንቀሳቀስ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል፡፡

2.1 አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሚያሟሉት መረጃዎች

ሀ. ግለሰብ ቆጣቢዎችና በአንድ ግለሰብ ስም የተመዘገቡ የንግድ ተቋማት

- የታደሰ የማንነት ማስረጃ፣

- የውጭ ዜጋ ለሆኑ የመኖሪያ ፈቃድ፣

- ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ

ለ. የግል የንግድ ተቋም

- የታደሰ የማንነት ማስረጃ፣

- የውጭ ዜጋ ለሆኑ የመኖሪያ ፈቃድ፣

- ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የኢንቨስትመንት ሰርትፊኬት፣

- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት(TIN)፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

ሐ. ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ

- ስልጣን ከተሰጠው አካል የተፈቀደ የምዝገባ ፈቃድ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የኢንቨስትመንት ሰርትፊኬት፣

- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት(TIN)፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የተፈቀደ የተመዘገበና ማህተም ያረፈበት Memorandom & Article of Association.፣

- በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ ግልጽ ያልሆነና አሻሚጉዳይ ሲያጋጥም በተቋሙ የህግ ባለሙያዎች የተገመገመበትና የህግ አስተያየት የተሰጠበት የጽሁፍ ማስረጃ፣

መ. የሽርክና ማህበር/Partnership/

- ስልጣን ከተሰጠው አካል የተፈቀደ የምዝገባ ፈቃድ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የኢንቨስትመንት ሰርትፊኬት፣

- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት(TIN)፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የተፈቀደ የተመዘገበና ማህተም ያረፈበት Memorandom & Article of Association.፣

- በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ ግልጽ ያልሆነና አሻሚ ጉዳይ ሲያጋጥም በተቋሙ የህግ ባለሙያዎች የተገመገመበትና የህግ አስተያየት የተሰጠበት የጽሁፍ ማስረጃ፣

ሠ. አክሲዮን ማህበር

- ስልጣን ከተሰጠው አካል የተፈቀደ የምዝገባ ፈቃድ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የኢንቨስትመንት ሰርትፊኬት፣

- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት(TIN)፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የተፈቀደ የተመዘገበና ማህተም ያረፈበት Memorandom & Article of Association.፣

- በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ ግልጽ ያልሆነና አሻሚ ጉዳይ ሲያጋጥም በተቋሙ የህግ ባለሙያዎች የተገመገመበትና የህግ አስተያየት የተሰጠበት የጽሁፍ ማስረጃ፣

ረ. የሙያ ማህበራት፣ እድሮችና ሌሎች የማህበራዊ ጉዳይ ማህበራት

- ስልጣን ከተሰጠው አካል የቀረበ የድጋፍ ደብዳቤ ወይም የምዝገባ ሰርትፊኬት፣

- እንደ አስፈላጊነቱ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የተፈቀደ የተመዘገበና ማህተም ያረፈበት Memorandom & Article of

Association.፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

ሰ. የሀይማኖት ተቋማት

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ከሀይማኖት ተቋሙ የበላይ ጠባቂዎች የተሰጠ የድጋፍ ማስረጃ፣

- እንደአስፈላጊነቱ ስልጣን ከተሰጠው የመንግስት አካል የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

ሸ. የውጭና የሀገር ውስጥ መያድ

- ከፍትህ ሚ/ር የተሰጠ ፈቃድ፣

- ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር የተሰጠ ፈቃድ(ለውጭ መያድ)፣

- ለውጭ ሀገር ዜጎች አንቀሳቃሾች የታደሰ የመኖሪያ ፈቃድ፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

ቀ. ህዝባዊ ድርጅቶች/Public Enterprise/

- ለምስረታው መነሻ የሆነው ነጋሪት ጋዜጣ፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

- የሂሳብ አንቀሳቃሾች የታደሰ መታወቂያ፣

- ፈራሚዎች ከሶስት ወር ወዲህ የተነሱት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣

- የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ያመለከቱበት ቅፅ'

ተ.ቁየብድር አይነት የእድገት ደረጃ መስፈርቶች ዝቅተኛ የብድር መጠን ከፍተኛ የብድር መጠን የብድር መክፈያ ጣራያ /በወራት / የወለድ መጠን የአገልግሎት ክፍያ ኢንሹራንስ
1 ጥቃቅን ብድር ጀማሪ - በጥቃቅን የጉሊት ስራ የተሰማሩ - ከብር 5000 በታች ካፒታል የሚጠይቅ ስራዎች 700.00 -ለእንዱስትሪ እስከ 50ሺ -ለአገልግሎት እስከ 30ሺ 24ወራት 10 % 2% 1%
ታዳጊ - በጥቃቅን የጉሊት ስራ የተሰማሩ - ከብር 5000 በታች ካፒታል የሚጠይቅ ስራዎች 700.00 -ለእንዱስትሪ እስከ 85ሺ -ለአገልግሎት እስከ 40ሺ 24ወራት 10 % 2% 1%
የበቃ - በጥቃቅን የጉሊት ስራ የተሰማሩ - ከብር 5000 በታች ካፒታል የሚጠይቅ ስራዎች 700.00 -ለእንዱስትሪ እስከ 100ሺ -ለአገልግሎት እስከ 50ሺ 36ወራት 10 % 2% 1%
2 አነስተኛ ብድር ጀማሪ - ቀደም ሲል ስራ የጀመሩ እና ካፒታላቸው ከብር 5000 በላይ የሚገመት ወይም ከብር 5000 በላይ መነሻ ካፒታል የሚጠይቅ ፡፡ - የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 700.00 -ለእንዱስትሪ እስከ 150ሺ -ለአገልግሎት እስከ 60ሺ 36ወራት 10% 2% 1%
ታዳጊ - ቀደም ሲል ስራ የጀመሩ እና ካፒታላቸው ከብር 5000 በላይ የሚገመት ወይም ከብር 5000 በላይ መነሻ ካፒታል የሚጠይቅ ፡፡ - የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 700.00 --ለእንዱስትሪ እስከ 500ሺ -ለአገልግሎት እስከ 200ሺ 36ወራት 10% 2% 1%
የበቃ - ቀደም ሲል ስራ የጀመሩ እና ካፒታላቸው ከብር 5000 በላይ የሚገመት ወይም ከብር 5000 በላይ መነሻ ካፒታል የሚጠይቅ ፡፡ - የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 700.00 በብሄራዊ ባንክ ጣሪያ መሠረት 36ወራት 10% 2% 1%
3 የግብርና ነክ ስራዎች ብድር ጀማሪ - የግብርና ስራዎች ላይ የተሰማሩ 700.00 እስከ 50 ሺ 24ወራት
10% 2% 1%
ታዳጊ - የግብርና ስራዎች ላይ የተሰማሩ 700.00 እስከ 100 ሺ 36ወራት
10% 2% 1%
የበቃ - የግብርና ስራዎች ላይ የተሰማሩ 700.00 እስከ 350 ሺ 36ወራት
10% 2% 1%
4 ማይክሮ ሊዝ ብድር - የንብረት፣የሰው ዋስትና ማቅረብ የማይችሉ - በተመረጡ የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ፣ - የጥበቃ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፣ - የማሽኑ ዋጋ 10 በመቶ በቅድሚያ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ/ች 700 በብሄራዊ ባንክ ጣሪያ መሠረት 36ወራት 10% 2% 2%
5 የአጭር ጊዜ ብድር - በአጭር ጊዜ ስራ ብድሩን ሊያስመልስ የሚችል መሆኑ የተረጋገጠ. 30000.00 በብድር ዙር እስከ 250ሺ 10 ወራት 2%/በወር - 1%
6 የቤት ግንባታና እድሳት ብድር -የሚገነባው/የሚታደሰው ቤት ባለቤትነት - ቋሚ ገቢ በቅጥር ወይም ከሌላ ምንጭ ያለው 700.00 -ለእንዱስትሪ እስከ 350ሺ 60 ወራት 11% 2% 2%
7 የተሸከተርካሪ ግዥ ብድር -የተሸከተርካሪ ግዥ ብድር - -እስከ 500ሺ 60 ወራት 11% 2% 1%
8 የግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ ብደር - በአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት መ/ቤቶች ቋሚ ሰራተኛ የሆነ - በቡድን ተደራጅቶ ብድር ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ -ከመስሪያቤታቸው የዋስትና ደብዳቤ ማፃፍ የሚችል 700.00 20 ሺ 24ወራት 11% 2% 1%


ማስታወሻ :- ከአጭር ጊዜ ብድር በስተቀር ሁሉም ብድር የሚከፈለው በየወሩ ነው፡፡