የዋስትና ሁኔታ

ተራ የቡድን ዋስትና

ተቋሙ ከሚጠቀምባቸው የዋስትና አማራጮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይኼውም እርስ በርስ በሚተዋወቁና ተመሳሳይ ወይም የተለያየ ስራ ለመስራት የሚፈልጉ ሰዎች በጋራ ተደራጅተው አንዱ ለሌላው ስለሚወስደው ብድር ሃላፊነት የሚወስድበት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ነጥቦች ማሟላት ይገባቸዋል፡-

 • የቡድን አባላት በቅርብ የሚተዋወቁና በራሳቸው ፍላጐት ተመራርጠው የተሰባሰቡ ስለመሆናቸው፣
 • የቡድን አባላት ቢቻል በአንድ ቀበሌ ወይም በአንድ የገበያ አካባቢ / የስራ ቦታ / የሚሰሩና ማህበራዊ ግንኙነት ያላቸው፤
 • የቡድን አባላት አንዱ ለሌላው ወይም ሁሉም ለአንዱ ወይም አንዱ ለሁሉም አባላት ኃላፊነት መውሰድ መቻላቸውን የተረጋገጠላቸው፤
 • ተገቢው የብድርና ቁጠባ ኮሚቴ አጣርቶ መልካም ተበዳሪ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው፣
 • በሥልጠና ቀናት በሙሉ የተሳተፋ፣
 • በተቋሙ ፖሊሲ መሠረት ተደጋጋሚ የሆኑ፣
 • በተራ የቡድን ዋስትና መሠረት ሥራቸው /ቢዝነሳቸው/ የተለያየ መሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ቋሚ የሥራ ቦታ በስማቸው ያላቸውና ቡድኑን በተመለከተ በልዩ ሁኔታ የተቋሙን ጠቀሜታ ከግንዛቤ በመውሰድ ይስተናገዳሉ፡፡
 • በቡድን ዋስትና እያንዳንዱ ቡድን የራሱ ቡድን መሪ ሊኖርው ይገባል፡፡

በመደበኛ ጠለፋ ዋስትና

መደበኛ የጠለፋ ዋስትና ማለት በቋሙ ፖሊሲ መሠረት የቡድን አባላት ተራ የቡድን ዋስትና ከመሠረቱ በኋላ እያንዳንዱ የቡድኑ አባል ለቡድኑም ተጠሪ የሚሆኑ ተጨማሪ ግለሰቦችን በዋስት የሚያቀርቡበት ወይም የቡድኑ አባል ያለበትን ዕዳ ለአባላቱ በወቅቱ ገቢ ወይም ተመላሽ ባያደርግ በእርሱ እግር በመተካት ተመላሽ ለማድረግ ቃል የሚገባበት የዋስት ዓይነት ነው፡፡

 • በተቋሙ ፖሊሲ መሠረት ለጠለፋ ዋስትና ከላይ በተቀመጠው የብድር ጣሪያ መሠረት ብድር ሊፈቀድ ይችላል፡፡
 • የጠለፋ ዋስትና አፈጻጸም ወይም በጠለፋ ዋስትና ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉት፡-
  • የደንበኛው የቤተሰብ ኃላፊ
  • በአካባቢ ተዋቂነት ያላቸው ግለሰቦች ፣
  • የክ/ከተማና የቀበሌ የወጣትና የሴት ማኀበር ፣
  • የመንግስት፣ የግል ድርጅት፣ወዘተ ሠራተኞች፤
  • ቀደም ሲል ቢዝነስ ያላቸው እና በአካባቢው የሚታወቁ ግለሰቦች ናቸው፡፡

በቡድን መሪ የጠለፋ ዋስትና

የዚህ ዓይነት የብድር ሥርዓት የቡድኑ አባላት ተራ የቡድን ዋስትና ከመሠረቱ በኋላ ከመሃከላቸው ቡድኑን ለመምራት ኃላፊነት የተሰጠው የቡድን ሰብሳቢ የሚያቀርበው ተጨማሪ ዋስትና / የጠለፋ ዋስትና / የሚጣራበት ነው:: በዚህ መሰረት የቡድን መሪው የቤት ባለቤት ከሆነ የቤት ባለቤትነት መረጃ ኮፒ፣ ነጋዴ ከሆነ የንግድ ፈቃድ፣ ተሽከርካሪ ወይም የሌሎች ማሽኖች ባለቤት ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ ማቅረብ የጠለፋ ዋስትና ውል በመሙላት ዋስ መሆን ይችላል፡፡ በስሙ ያሉ ለዋስትና የሚያገለግሉ ተንቀሳሽም ሆነ ያልሆነ ንብረት ባለቤት ካልሆነ የሌላ ሶስተኛ ወገን ማቅረብ ይችላል፡፡

የመሣሪያዎች ሊዝ ብድር ዋስትና

ዝርዝሩ ከላይ በተራ ቁጥር 6.2 በተቀመጠው መሰረት ሆኖ እንደ ዋስትና የሚያገለግለው በዋነኛነት የሚገዛው የስራ መሣሪያ /ማሽን/ ነው፡፡

የደመወዝ ዋስትና

በደመወዝ ዋስትና የሚሠጠው የብድር መጠን ከብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ/ አይበልጥም፡፡ነገር ግን በተቋሙ ውስጥ በግል በተዳሪነት ከሁለት እና ከዛ በላይ ብድር የወሰዱ እና በደሞዝ ዋሰትና ጣሪያ ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ/ የወሰዱ እና በአከፋፈላቸው የታመነባቸው እስከ ብር 5,000.00/ሃምሣ ሺህ/ በደሞዝ ዋስትና ማበደር ይቻላል፡፡ ዝርዝሩ በአፈፃፀም መመሪያው ላይ በተቀመጠው መልኩ ይሆናል፡፡

የንብረት ዋስትና

የንብረት ዋስትና ማለት በተቋሙ የብድርና ቁጠባ ፖሊሲ መሠረት በደንበኞች ለሚወሰድ የብድር ገንዘብ በዋስትና መMክ የሚሰጥ መያዣ ንብረት ነው፡፡

 • ቤት
  ደንበኞች የራሳቸውንም ሆነ የሶስተኛ ወገን ቤት ስለሚወሰዱበት የብድር ገንዘብ መመለስ ማረጋገጫ በመያዣነት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመያዣነት የሚቀርብ ቤት ስንጠቀም የሚከተሉት ከግምት ዉስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
  • የቤቱ ግምት መጠን ከግማሽ በላይ /50%/ ከብድሩ መብለጥ አለበት፡፡
  • በመያዣነት የቀረበው ንብረት በአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር የታወቀና መታገድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 • ተሽከርካሪ
  በተቋሙ የብድር ፖሊሲ መሠረት ደንበኞች በራሳቸውም ሆነ በሌላ ሶስተኛ ወገን ተሽከርካሪ ዋስትና በማስያዝ የብድር ገንዘብ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡ ሆኖም የሚከተሉት መመዘኛዎች መካተት አለባቸው፡-
  • ተሽከርካሪው በአካል ሲታይ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ መሆኑ የተረጋገጠ፣
  • ተሽከርካሪው አዲስ አበባ ከተመዘገበ ከ1ዐ ዓመት ያላለፈው መሆን አለበት፡፡
  • በተቻለ መጠን ተሽከርካሪው አዲስ አበባ ወይም የፌደራል መ/ቤት የተመዘገበ ወይም በኦሮሚያ ክልል ሆኖ በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት ምዝገባ ያጠናቀቀ መሆን አለበት፣
  • የተሽከርካሪው የዋጋ ግምት በመዝጋቢው አካል የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡
 • የማሽን ዋስትና
  በተቋሙ ፖሊሲ መሠረት ደንበኞች በራሣቸው ማሽንም ሆነ በሌላ ሶስተኛ ወገን ማሽን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም የሚከተሉት ፍሬ ነገሮች በዝርዝር መታወቅ ይገባቸዋል፡
  • ማሽን ሲያዝ ሁልጊዜም በጣምራነት ግለሰቡ/ድርጅቱ/ ያለው መደwርም በዋስትና ይያዛል፤
  • የማሽኑን ወቅታዊ ዋጋ ከንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በማስገመትና ይህንኑ ለሶስተኛ ወገን እንዳይሸጥ፤ እንዳይለወጥ ማስደረግ የገባል፡፡
  • እንዲሁም መንግስታዊ ተቋም የጥበቃ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ አለያም የሚያስከትለውን ወጪ ለመሸፈን ዝገጁ የሆኑ
  • ማሽኑ የተገዛበት ጊዜ እጅግ ቢዘገይ ከ5 ዓመት በፊት መሆን የለበትም፡፡

የተከፈለ ወይም ተቀማጭ የሆነ ገንዘብ ዋስትና

 • በተቋሙ ቁጠባ መሰረት ተቀማጭ ያደረገ ደንበኛ ቢኖርና ይኸው የቁጠባ ገንዘብ እንዳይወጣ በማሳገድ ተቀማጭ የሆነውን የገንዘብ መጠን እስከ 125% (በመቶ) ድረስ የብድር ገንዘብ መበደር ይቻላል፡፡ በዚህን ግዜ ደንበኛው ስለገንዘቡ መታገድ የስምምነት ውለታ በቅድሚያ መፈራረም ይኖርበታል፡፡
 • በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ - በልዩ ልዩ ምክንያት፤ መሬት በሊዝ ለመውሰድ ወይም የመኖሪያ ቤት ለመስራት በማሰብ የቅድሚያ ክፍያ ተቀማጭ ያላቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ይኸው ገንዘባቸው ከተቋሙ ደብዳቤ ሣይፃፍ/ክሊራንስ ሣይገኝ/ እንዳይለቀቅ በማሳገድ የተቀማጩን 75% ያህል የብድር ገንዘብ ማበደር ይቻላል፡፡
 • ለእቁብ የተከፈለ ገንዘብ - በአንድ በታወቀ ለእቁብ የተከፈለ ገንዘብ አገልግሎቱም በአግባቡ እየከፈሉ ስለመሆናቸው የተረጋገጠላቸው የእቁብ አመራሮች በሚወስዱት ኃላፊነትና ውለታ መሠረት በብድሩ ቀን/ዕለት/ ክፍያ የተደረገበት የእቁብ ገንዘብ መጠን 75% ያህል የብድር ገንዘብ ማበደር ይቻላል፡፡ ይህንን የዋስትና አይነት ለመጠቀም በቅድሚያ ደንበኛው መደበኛ የእቁብ ከፋይ ስለመሆኑ ከሚታይ የእቁብ መመዝገቢያ መዝገብና ከአስተባባሪያዎቹ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የእቁቡ ኃላፊዎች በሚፈርሙት ተጨማሪ ሃላፊነት የመውሰድ ውለታ መሰረትና የእጣው ገንዘብ እገዳ መሰረት ብድሩ ይፈቀዳል፡፡
 • የአለኝታ ገንዘብ (Receivables) - በአንድ በታወቀ የመንግስት ወይም የግል ድርጅት በተለያየ ምክንያት ያልተሰበሰበ ፤በተለይም ሥራ ሰርተው አስረክበው ገንዘብ ያልተከፈላቸው ሲኖርና የከፋይ ድርጅት የመክፈል አቅምና በተቋሙ የመክፈል ስምምነት በተረጋገጠ ጊዜ ተበዳሪው ያለውን የቢዝነስ ዋስትና ግምት ዉስጥ በማስገባት ያልተከፈለውን ገንዘብ 75 %(በመቶ) ያህል መበደር ይቻላል፡፡
 • ወደፊት በሚከፈል ገንዘብ የሥራ ውልን መሠረት ያደረገ ዋስትና - የተቋሙ ነባር ደንበኞች የሆኑና በብድር አመላለሳቸው፣ በስነ ምግባራቸው ጥሩ የሆኑ፣ ከመንግስት ድርጅት ወይም ከግል ድርጅት የሥራ ውል መረከባቸው የተረጋገጠላቸውና ካላቸው የቢዝነስ ዋስትና በተጨማሪ ለአጭር ጊዜ ብድር እስከ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ድረስ ድርጅቱ በቀጥታ ለተቋሙ እንደሚያስገባ በሚደረግ ስምምነት መሠረት ተገቢውን የዋስትና ውል በማስገባት ብድር መበደር ይቻላል፡፡
 • የቦታ ሊዝ ዋስትና - ለተለያየ የቢዝነስ ሥራ ከመንግስት መሬት በሊዝ የወሰዱና ለሊዝ ዘመኑ በቅድሚያ ክፍያ የከፈሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የብድር ገንዘብ በወቅቱ ካልከፈሉ ተቋሙ ቦታውን ለሌላ ሶስተኛ ወገን መልሶ መጠቀም እንደሚቻልና ይኸው ቦታ የሚኖረው የገበያ ሁኔታና የብድር መጠኑ ግምት ውስጥ በማስገባት የመሬት አስተደደር ፈቃደኝነቱን ሲገልጽ በዋስትና በመያዝ ማበደር ይቻላል፡፡

የቼክና ጣምራ ዋስትና

ለአጭር ጊዜ ሥራ ማስኬጃ ብድር ወደፊት የሚከፈል ቼክና ተሽከርካሪ ወይም የደመወዝ ዋስትና እንዲሁም የማሽን ዋስትና ወይም የቢዝነስ ዋስትና በመጠቀም የብድር ገንዘብ መበደር ይቻላል፡፡

የት/ቤት ማስረጃና የቤተሰብ ጣምራ ዋስትና

በቴክኒክና ሙያ በዲኘሎም ወይም በዲግሪ የተመረቁ ሆነው በሙያቸው ለመሥራት የቦታ፣ የሥልጠና ወዘተ... ዝግጅት ያደረጉ ሙያተኞች  የትምህርት ማሥረጃቸውን ከቤተሰቦቻቸው የጣምራ ዋስትና ጋር በማቅረብ እስከ ብር 5ዐዐዐ መበደር ይቻላል፡፡ ሆኖም የሙያ ማስረጃቸው በሚመለከተው የትምህርት ተቋም የታገደና ስምምነቱን የሰጠ መሆኑ ማረጋገጫ መቅረብ  ይገባዋል፡፡ የትምህርት መረጃውን ቀደም ብለው የወሰዱ ከሆነ ዋናውን ለተቋሙ ዘንድ እንዲያስቀምጡ ለማድረግና መረጃውን ለሚሰጠው አካል በድጋሚ እንዳይወጣ ማረጋገጫ በመቀበል ማስተናገድ ይቻላል፡፡

የቢዝነስ ዋስትና

 • የተቋሙ ነባር ደንበኞች የሆኑና በአግባቡ እየከፈሉ የነበሩ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ የሚገኙ ነባር ደንበኞች ለሶስተኛ ወገን እስከ ብር 5ዐዐዐ የብድር ገንዘብ ለሶስተኛ ወገን ዋስትና ገብተው መበደር ይችላሉ፡፡
 • በተከታታይ ከተቋሙ የብድር አገልግሎት አግኝተው በአግባቡ የከፈሉ በታማኝነት የሚታወቁ ካፒታላቸው ከብር 5ዐ,ዐዐዐ/ሃምሳ ሺ/ ያላነሰ ደንበኞች የንግድ መደብራቸውን ፣ያለውን ማሽን፣ ጥሬ ዕቃ ምርት፣የድርጅቱን ስም ወዘተ… በዋስትና በማስያዝ ለመጀመሪያ ጊዜ እስከ ብር 1ዐ,ዐዐዐ/አስር ሺ/ ለአጭር ጊዜ መበደር ይችላል፡፡
 • ቀደም ሲል ሠፊ የሥራ እንቅስቃሴ ያላቸው፤ ይህንንም የሚያረጋግጥ የገንዘብ ፍሰትና የሥራ ሁኔታማሳየት የሚችሉና ካፒታላቸውም ከ1ዐዐ,ዐዐዐ ብር/አንድ መቶ ሺ ብር/ ያላነሰ ስለመሆኑ  መረጃ ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ባላቸው የንግድ መደብር ዋስትና መሠረት እስከ ብር 1ዐ,ዐዐዐ/አስር ሺ/ የሚሆን የአጭር ጊዜ ብድር ለመጀመሪያ ጊዜ መወሰድ ይችላሉ፡፡

የኢንሹራንስ ቦንድ

ከታወቀ የኢንሹራንስ ተÌም የሚቀርብ የዋስትና ማረጋገጫ ለአጭር ግዜ ብድር እስከ 75 በመቶ የብድር ገንዘብ መፍቀድ ይቻላል፡፡ ሆኖም በቅድሚያ የኢንሹራንስ አገልግሎቱ የሰጠው ዋስትና አስተማማኝና የብድሩ ገንዘብ በወቅቱ ባይከፈል ኩባንያው ለተkሙ ገቢ ሰለማድረጋቸው በፅሁፍ ማረጋገጥ ይገባል፡፡

የተቋማት ዋስትና

 • የህብረት ሥራ ማህበራት - ነባር የህብረት ሥራ ማህበራት በንብረታቸው ዋስትና አባሎቻቸው ለሚያካሂዱት ሥራ የሚያስፈልጋቸውን የብድር ገንዘብ እንዲያገኙ ማድረግ ይችላሉ፡፡በተጨማሪም ማህበሩ በቢዝነሱ ዋስትና በመግባት መበደር ይችላል፡፡
 • እድሮች
  • ህጋዊ እውቅና ያላቸው እድሮች ከተቋሙ ጋር በሚያደርጉት ስምምነት አባሎቻቸው ለሚወስዱት የብድር ገንዘብ ዋስትና መስጠት ይችላሉ፡፡
  • በተቋሙ የቁጠባ ሂሣብ ያላቸው እድሮች ባላቸው ቁጠባ ዋስትና መስጠት የሚችሉ ሲሆን ካላቸው የቁጠባ ገንዘብ 75 % መብለጥ የለትም፡፡
  • የእድሮቹ አመራር በቅድሚያ ስለአባላቱ ዝርዝር መግለጫና ዋስትና ሰለመውሰዳቸው የሚገልፅ በማረጋገጫ ደብዳቤ መግለፅ ይጠበቅበታል፡፡
  • በእድሩ ስልጣን ያለው አካል የዋስትና ውለታ የመፈረም ገዴታ አለበት፡፡
  • ለውለታው ይረዳ ዘንድ የእድሩን ህጋዊ ማህተም ግዴታ መጠቀም ይገባል፡፡
 • መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ህዝባዊ ማህበራት - ድርጅቶቹ ከተቋሙ ጋር በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት ዋስትና ሲገቡ መበደር ይችላሉ፡፡ ዋስትና የሚወሰደው እንደ ድርጅት በመሆኑ በተቋማቱ ውለታ የመፈፀም ስልጣን ያላቸው ኃላፊዎች ብቻ በሚገቡት የውል ስምምነት መሰረት ብቻ የሚፈፀም ይሆናል፡፡