ተቋሙ የኮርባንኪንግ ሲስተምን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኙን ምዕራፍ ተያይዟል፡፡ አዲስ የብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍና የመረጃ አያያዙን ለማዘመን የሚረዳውን የኮር ባንኪንግ ሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ተቋሙ በተያዘው 2010 ዓመት አጋማሽ ላይ የኮር ባንኪንግ ሲሰተሙን ለመተግበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን በአሁን ሰዓት ለአቅራቢዎች በአለም አቀፍ ጨረታ ግዥ አሰራር መሰረት የጨረታ ጥሪ አድርጓል፡፡
የኮር ባንኪንግ ሲስተም ግዢ ጨረታው በኢትዬጲያን ሄራልድ፣ በፎርቹን እና ሪፖርተር ጋዜጦች ከ22/07/2010 ቀን ጀምሮ አየር ላይ የዋለ ሲሆን፣ከ24/07/2010 ጀምሮ ላሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ይከናወናል። በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም አሸናፊው ድርጅት እንደሚለይ የተያዘው የፕሮጀክት እቅድ ያሳያል፡፡ ሲስተሙ ተግባራዊ ሲደረግ ለደንበኞች ፈጣን አገልግሎት በመስጠት እርካታን ለመጨመርና የመረጃ አያያዙን በማዘመን ረገድ የተሸለ በመሆን ለተቋሙ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ከላይ የተጠቀሱ ጋዜጦች መመልከት ወይንም በተቃሙ ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት አልያም በስልክ
ቁጥሮች 011-126- 26-85/011- 126-31- 48 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።