የብድር አገልግሎት እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ማንኛውም የተቋሙን አገልግሎት የሚፈልግ ግለሰብ ቡድን/ማህበር ወይም ድርጅት የአገልግሎት ጥያቄውን የሚያቀርበው በሚኖርበት የቀበሌ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያ ነው፡፡

ሆኖም ግለሰቡ ወይም ቡድኑ የሚሠራበት አካባቢ የተለየ ቀበሌ በሆነ ጊዜ ነዋሪ ከሆነበት ቀበሌ የነዋሪነትና ብድር አለመውሰዱን የሚያረጋግጥ መረጃ በማግኘት ወደሚሰራበት ቀበሌ እንዲተላለፍ ማድረግ ያስፈልጋል። በሌላም በኩል ደንበኞች ዋናው መስሪያ ቦታቸው ከመኖሪያ ቦታቸው የተለየ በሆነ ጊዜ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት በሚሰሩበት ቦታ ወይም ፈቃድ ያገኙበት ክ/ከተማ ወይም ቀበሌ መሆን ይገባዋል።

የብድር ጥያቄ መመዘኛ መስፈርቶች

ማንኛውም ብድር ጠያቂ የሚከተሉትን መመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል

 • የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑ፤
 • በከተማው ውስጥ በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች የተሰማሩ ወይም ለመሰማራት ዝግጅት ያደረጉ፣
 • በኢትዮጵያ ህግ መሠረት ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች፣
 • እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ግለሰቦች
 • በህገ ወጥ የንግድና በአገልግሎት ያልተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች፣
 • ከቴክኒክና ሙያ ተመርቀው በማህበር/በግል/ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑ፣
 • የተቋሙን ፖሊሲና ያሠራር መመሪያ ተቀብለው ለመተግበር ዝግጁ የሆኑ፣
 • ቋሚ የሥራ ቦታ ያላቸው ወይም ሥራቸው ተንቀሳቃሽ ከሆነም ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
 • ከብር 5,ዐዐዐ በላይ ብድር የጠየቁ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ለሥራው በቂ ልምድ ወይም ወደሥራው ለመግባት የሚያስችል ግንዛቤ ያላቸው፣
 • ጥሩ ስነምግባር ያላቸው፣
 • ምንም ዓይነት ብድር የሌለባቸው መሆኑ ወይም ከዚህ በፊት ተበድረው በመጥፎ አከፋፈል የማይታወቁ
 • ብድር ጠያቂዎቹ በቡድን የተደራጁ ከሆነ አባላቱ እርስ በእርስ የሚተዋወቅ እና አንዳቸው ለአንዳቸው ኃላፊነት የሚወስዱ
 • የተቋሙን የብድር ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ለማክበር ፈቃደኛ የሆኑ
 • በህብረት ሽርክና ወይም በማኅበር የተደራጁ ከሆነ አግባብ ካለው የመንግስት ተቋም ፈቃድ ያገኙ
 • የድርጅቱ ባለቤቶች በግል ወይም በቡድን ቀደም ሲል ብድር ያልወሰዱ ወይም ወስደው ያጠናቁቁ ስለመሆናቸው ከመኖሪያ ቀበሌያቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ማህበር ከሆነ የድርጅቱን አመሠራረትና አመራር የሚገልጽ በህጋዊ የመንግስት ተቋም የተረጋገጠ ሰርትፍኬት መተዳደሪያ ደንብ ያላቸው፣
 

መሰረታዊ መረጃዎች

የብድር አገልግሎት እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ማንኛውም የተቋሙን አገልግሎት የሚፈልግ ግለሰብ ቡድን/ማህበር ወይም ድርጅት የአገልግሎት ጥያቄውን የሚያቀርበው በሚኖርበት የቀበሌ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያ ነው፡፡

ዝርዝር ንባብ...