አባል ይሁኑ

ከማይክሮ ባንክ ለመጠቀም እባክዎትን ይህን ይጫኑ


2.2 የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ከማንኛውም የብድር አገልግሎት ደንበኞች በመሰረታዊነት የሚጠበቁ መስፈርቶች የሚከተሉት ሆኖ እንደ ብድር አገልግሎት አይነት ከታች የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ይጠበቃሉ፡

1. ነዋሪነታቸውና የስራ አካባቢያቸው በአዲስ አበባ ከተማና ተቋሙ በሚሰራባቸው አካባቢዎች የሆነ፡

2. እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ግለሰቦች፡

3. በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎች የተሰማሩና ለመሰማራት ዝግጁ የሆኑ፡

4. በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራዎችየተሰማሩ ከሆነ ደረጃቸውን የሚያሳይ (የሚገልፅ) ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ሌሎች ከሆኑ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የሚያቀርቡ፡

5. ቋሚ የሥራ ቦታ ያላችው ወይም ሥራቸው ተንቀሳቃሽ ከሆነ ይህንን የሚያሳይ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡

6. የብድሩን ከ15-30 በመቶ በቅድሚያ የሚቆጥቡ የብድር ተጠቃሚዎች መሆን ይችላሉ እንዲሁም የአጭር ጊዜ ተበዳሪዎች ቅድመ ብድር ቁጠባው የብድሩን 2 በመቶ በመቆጠብ የብድር ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

7. በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ስለመሆኑ አግባብ ካለው የመንግስት ተቋም ፈቃድ ያገኙ የንግደ ድርጅቶች፣ የሕብረት ስራ ማህበራት፣ ዕድሮችና የብዙሀን ማህበራት፡

8. የተሰማሩበት ስራ ሕጋዊና በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የለው፡

9. የድርጅት ባለሀብቶች በግልም ሆነ በቡድን ቀደም ሲል ብድር ያልወሰዱ ወስደውም ከሆነ በአግባቡ የመለሱና ለዚህም ማረጋገጫ ከመኖሪያና ከመስሪያ ቦታቸው የሚያቀርቡ፡

10. ምንም ዓይነት ብድር የሌለባቸው ወይም በመጥፎ አከፋፈል የማይታወቁ እና ብድርና ቁጠባ አገልግሎት መስጫ ከአንድ ጊዜ በላይ ከዲስትሪክትና ከዲስትሪከት ንኡስ ቅ/ጽ/ቤት ብድር ያልወሰዱ'ብድር ወስደውም ከሆነ ሙለ በሙሉ ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡

11. ደንበኞች ለሚበደሩት ብድር ተመጣጣኝ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡

12. የብድር ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችና ዋሶቻቸው ህጋዊ የጋብቻ ሁኔታ ማስረጃ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡

13. የብድር ደንበኞች ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት 2 ጉርድ ፎቶ ማቅረብ

14. የተቋሙን ደንቦች፣ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች ተቀብለው ለመተግበር ዝግጁ የሆኑ፡


ሀ. የረጅም ጊዜ ብድር

• የብድር ጠያቂው የብድር ጥያቄውን በመስሪያ ወረዳው ማመልከት ፡

• የብድር ጠያቂው የብድር ጥያቄውን በመስሪያ ወረዳው ማመልከት

• ብድር ጠያቂው አዲስ ስራ የሚጀምር ከሆነ በየወሩ ለስድስት ወራት የቁጠባ ደንበኛ በመሆን የብድሩን 20 በመቶ ቅድመ ብድር ቁጠባ መቆጠብ ወይም ነባር ስራ ላይ የተሠማራ ከሆነ በአንድ ጊዜ 20 በመቶ ቅድመ ብድር ቁጠባ መቆጠብ

• የብድር ጠያቂው የብድር ጥያቄውን በመስሪያ ወረዳው ማመልከት

• የብድር ዕዳ እንደሌለበት የሚያረጋግጥ ክሊራንስ መያዝ

• የብድር ማመልከቻ/የሥራ ዕቅድ ማቅረቢያ/ መሙላት

• ከግብርና ጋር የተያያዙ ስራዎች እስካልሆኑ ድረስ ከብር 5,000 በላይ የንግድ ፈቃድ የመስሪያ ቦታ ማረጋገጫ/የመስሪያ ቦታው የራሱ ወይም የኪራይ የተገኘ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ስምምነት) ማቅረብ

• በብድሩ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቁ ናቸው፡፡

ለ. የአጭር ጊዜ ብድር

• የብድር ጠያቂው የብድር ጥያቄውን በመኖሪያ ወረዳው ማመልከት

• የብድር እዳ እንደሌለበት የሚያረጋግጥ ክሊራንስ ደብዳቤ መያዝ

• የብድር ማመልከቻ/የሥራ ዕቅድ ማቅረቢያ/መሙላት

• የንግድ ፈቃድ፣ የመስሪያ ቦታ ማረጋገጫ (የመስሪያ ቦታው የራሱ ወይም በኪራይ የተገኘ ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ስምምነት ማቅረብ

• ለብድሩ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ

• የብድሩን ሁለት በመቶ ቅድመ ብድር ቁጠባ መቆጠብ፡

ሐ. የተሽከርካሪ ግዥ ብድር

የዚህ ብድር ዓላማ ነዋሪዎች የሃበት ባለቤት የሚሆኑበትንና የሃበት ክፍፍል ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ ረገድ ተቋሙ የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሲሆን ከተጠቃሚዎች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታ ይጠበቃል፡

• ለሁለት አመት የብድሩ 30 በመቶ ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ በየወሩ ቁጠባ መቆጠብ

• ለራሱ ፈቃደኝነት ተሽከርካሪውን መምረጥና ተቋሙ እንዲገዛለት መጠየቅ

• የብድር መክፍል አቅሙ አስተማማኝ የሆነ

• ከብር 1500 ያላነሰ አንድ የሰው ዋስትና ማቅረብ

መ. የቤት ግንባታና እድሳት

የዚህ ብድር ዓላማ መሰረቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች በዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ሁኔታ መደገፍ ሲሆን የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ይጠበቃሉ፡፡

• ለአንድ አመት የብድሩ 30 በመቶ ተመጣጣኝ ለሆነ ሁኔታ በየወሩ ቁጠባ መቆጠብ

• የሚገዛለት ወይም የሚገነባውና የሚታደሠው ቤት ለተቋሙ የአገልግሎት ክልል ውስጥ የሆነ

• የግንባታ/ዕድሳት ብድር ከሆነ ከከተማው አስተዳደር የግንባታና እድሳት ፈቃድ ያለው ወይም ፈቃዱ ከወጣ ጊዜው ያላለፈ

• የብድር መክፈል አቅሙ አስተማማኝ የሆነ

• ከብር 1500 ያላነሠ አንድ የሰው ዋስትና ማቅረብ