ስለ እኛ - የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ኃላፊነት
የፅሁፍ ቃላት ማዉጫ
ስለ እኛ
የሥራ አመራር ቦርድ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ኃላፊነት
ሁሉም ገፅ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ኃላፊነት

 • የዳይሬክተሮች ቦርድ በንግድ ህግ ከመመስረቻው ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ፣ እንዲሁም በጠቅላላው ጉባዔ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
 • የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚከተለው ስልጣን አለው፣
  • የድርጅቱን አስተዳደር መቆጣጠር
  • በጠቅላላ ጉባዔ የተላለፈውን ውሳኔ እንደጠበቀ ሆኖ የተቋሙን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ
  • በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የተዘጋጀውን የሰራተኛ ቅጥርና የአስተዳደር ፖሊሲ ማጽደቅ
  • ገንዘብ መበደር፣ ማበደር፣ ዕዳን መክፈል እና የገንዘብ ሰነድ ማሳተም
  • ከፍርድ ቤት ክርክር ውጭ ውዝግቦችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣኑን በሙሉ ወይም በከፊል ለሰብሳቢው ወይም ለማናቸወም የተሾመ የኩባንያው አባላት ሊሰጥ ይችላል
 • ቦርዱ በንግድ ህግ አንቀጽ 362፣363 እና 364 ላይ የተጠቀሰው ሥልጣንና ተግባር ይኖራዋል
 • ቦርዱ ዋና ሥራ አስኪያጁና ለርሱ ተጠሪ የሆኑትን ኃላፊዎች የመሰየምና የማሰናበት ስልጣን አለው