ስለ እኛ
የፅሁፍ ቃላት ማዉጫ
ስለ እኛ
የሥራ አመራር ቦርድ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ኃላፊነት
ሁሉም ገፅ

የተቋሙ ራዕይ

በ2012 ዓ.ም ቀጣይነቱንና አስተማማኝነቱን ያረጋገጠና በሃገሪቱም ሆነ በአፍሪካ ሞዴል የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋም መሆን፡፡

የተቋሙ ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ እና ተቋሙ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ውስጥ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተሰማሩ ተቋማት በተለይም ለሴቶች ትኩረት በመስጠት ቀጣይነትና አስተማማኝነት ያለው የፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ ድህነትና ስራአጥነትን መቅረፍ ፡፡

የተቋሙ እሴቶች (Core values)

 • ግልፅነት
 • ተጠያቂነት
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን
 • በእውቀትና በእምነት እንመራለን
 • ቅድሚያ ለደንበኞች መስጠት
 • ቁጠባን እናበረታታለን
 • አሳታፊነት

የተቋሙ ድርጅታዊ መዋቅር

ተቋሙ በየጊዜው የሚኖረውን የተገልጋይ ፍላጎትና ወቅቱ የሚፈልገውን የገበያ ውድድር ታሳቢ በማድረግ የመዋቅር ማሻሸያ ያርጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በ2009 ዓ.ም ተግባራዊ በተደረገው የተቋሙ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሰረት፡ ከማኔጅንግ ዳይሬክተር ጽ/ቤት በተጨማሪ በሁለት ዘርፎች፤ በአንድ መምሪያና በስምንት ዋና ዋና አገልግሎት ክፍሎች በመዋቀር ከማእከል ዋና መ/ቤት በወረዳ ደረጃ እስካለው ንዑስ ዲስትሪክት ጽ/ቤት መዋቅሩን በመዘርጋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን በሚከተሉት የሚታዩ ናቸው፡፡

በተቋሙ የሚገኙ ዋና ዋና ክፍሎች

 • ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጽ/ቤት
 • ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኦፕሬሽን ዘርፍ
 • ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የፋ/ሶስተኛ ወገን ገንዘብ አስተዳደር ዘርፍ
 • የሰው ኃይል ልማትና ሀብት አስተዳዳር መምሪያ
 • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት
 • የገበያ ጥናትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት አገልግሎት
 • የእቅድና የለውጥ መሳሪያዎች አገልግሎት
 • የዉስጥ ኦዲት አገልግሎት
 • የሪስክና ኮምፕሊያንስ አገልግሎት
 • የሞባይልና ወኪል ባንኪንግ አገልግሎት
 • የህግ አገልግሎት
 • የማይክሮ ኢንሹራንስ አገልግሎት

የተቋሙ ባለአክስዮኖች

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
 • የአዲስ አባባ ከተማ ወጣቶች ማህበር
 • የአዲስ ሴቶች ማህበር
 • ካራ ሃሎ የገበሬዎች ህ/ስራ ማህበር
 • ሁለት የግል ባለአክስዮኖች
 • አዲስ አበባ ከተማ ማምህራን ማህበር
 • አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
 • አዲስ አበባ ከተማ አንበሳ አውቶቡስ
 • አዲስ አበባ ከተማ ኤግዝቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ኢንተርፕራይዝ

የተቋሙ የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች

የተቋሙ አገልግሎቶች በተጠቃሚውና በባለድርሻ አካላት ዘንድ ግልጸኝነት ኖሮት ተቋሙ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ያሰፈነ እንዲሆን በአገልግሎቶቹና አገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ በመደበኛና እንዳስፈላጊነቱ በየጊዜው የጋራ ውይይት የሚያርጉ የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች የተለዩ ሲሆን እነሱም፡-

 • የደንበኞች አማካሪ ምክር ቤት
 • የወጣት አደረጃጀቶች
 • የሴት አደረጃጀቶች በዋናነት ተቋሙ በህዝብ ክንፍ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡
 • ተቋሙ በማቋቋሚያ አዋጁ ቁጥር 40/1988 እና ማሻሻያ አዋጁ ቁጥር 626/2001 መሰረት የሚከተሉት ተግባራት ተሰጥቶታል
  • የውዴታም ሆነ የግዴታ ቁጠባ በተጠየቀ ግዜ የሚከፈል እንዲሁም ጊዜ ገደብ ተቀማጭ መቀበል።
  • በገጠርና በከተማ በግብርናና በሌሎች ስራዎች እንዲሁም በገጠርና በከተማ በጥቃቅንና አነስተኛ መስኮች ለተሰማሩ ሰዎች ብድር መስጠት
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ተከፋይ የሚሆኑ የሀዋላ ወረቀቶችን ማውጣትና መቀበል፡፡
  • ብሄራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት አነስተኛ የመድህን ስራ መስራት
  • ዓላማቸው ገቢ ማስገኘት የሆነ እንደ ግምጃ ቤት ሰነዶችና ሌሎች የአጭር ጊዜ የንግድ ወረቀቶችን ብሄራዊ ባንክ በሚወስነው መሰረት መግዛት
  • በንብረቱ ዋስትና ወይም በሌላ አኳኋን ለድርጅቱ ሥራ የሚውል ገንዘብ መበደር፡፡
  • ሥራውን የሚያከናውንባቸውን ሕንፃዎች ጨምሮ ማናቸውንም የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት በባለቤትነት መያዝ፣ መንከባከብና ለሌሎች ማስተላለፍ፡፡
  • በከተማና በገጠር በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ መስኮች የተሰማሩ ሰዎች የሚያካሂዱትን ገቢ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶችን ማገዝ
  • ለደንበኞች የአመራር የገበያ የቴክኒክ እና አስተዳደራዊ ምክር መስጠትና በእነዚህም መስኮች አገልግሎቶች ለማግኘት እንዲችሉ ማገዝ
  • ለጥቃቅንና ለአነስተኛ የንግድ ስራዎች ዓላማ የሚውል ገንዘብ ማስተዳደር
  • ለአነስተኛ ብድር ለሚቀርብ ሰፊ ዓላማ የሚውል ገንዘብ ማስተደደር

  የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት

  >

  ስም ኃላፊነት ፎቶግራፍ

  1.       አቶ ዲላሞ ኦቶሬ

  ሰብሳቢ
  አቶ አማረ ሽበሽ አባል
  ው/ሮ አልማዝ አብረሃ አባል
  አቶ ሀረጎት አለሙ አባል
  አቶ ኤርሚያሰ ማትያስ አባል

  1.       አቶ ውብነህ እምሩ

  አባል
  አቶ
  አባል

  የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ኃላፊነት

  • የዳይሬክተሮች ቦርድ በንግድ ህግ ከመመስረቻው ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ፣ እንዲሁም በጠቅላላው ጉባዔ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚከተለው ስልጣን አለው፣
   • የድርጅቱን አስተዳደር መቆጣጠር
   • በጠቅላላ ጉባዔ የተላለፈውን ውሳኔ እንደጠበቀ ሆኖ የተቋሙን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ
   • በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የተዘጋጀውን የሰራተኛ ቅጥርና የአስተዳደር ፖሊሲ ማጽደቅ
   • ገንዘብ መበደር፣ ማበደር፣ ዕዳን መክፈል እና የገንዘብ ሰነድ ማሳተም
   • ከፍርድ ቤት ክርክር ውጭ ውዝግቦችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣኑን በሙሉ ወይም በከፊል ለሰብሳቢው ወይም ለማናቸወም የተሾመ የኩባንያው አባላት ሊሰጥ ይችላል
  • ቦርዱ በንግድ ህግ አንቀጽ 362፣363 እና 364 ላይ የተጠቀሰው ሥልጣንና ተግባር ይኖራዋል
  • ቦርዱ ዋና ሥራ አስኪያጁና ለርሱ ተጠሪ የሆኑትን ኃላፊዎች የመሰየምና የማሰናበት ስልጣን አለው